የአምቦ የገ/ህ/ ሥራ ዩኒዬን ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ ማዕከላዊ መጋዘን ያከማቸውን በቆሎ ብዛት 11,500 ኩንታል እንዲሁም 400 ኩንታል ነጭ ገብስ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የእህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአምቦ የገ/ህ/ ሥራ ዩኒዬን ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ ማዕከላዊ መጋዘን ያከማቸውን በቆሎ ብዛት 11,500 ኩንታል እንዲሁም 400 ኩንታል ነጭ ገብስ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾቹ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከዩንየኑ ገበያ ክፍል በ500 ብር መግዛት ይችላሉ።
2. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾቹ የበቆሎውን ሁኔታ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ በዩኒየኑ መጋዘን በስራ ሰዓት ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ከግዥ ውስጥ የሚታሰብላቸው ይሆናል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን በ5፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
6. ተጫራቾች /ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠየቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታው አሸናፊ በገባው ውል መሰረት ከፍያ አጠናቆ ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል። አሸናፊው በተሰጠው ቀናት ውስጥ ያላነሰ እንደሆነ ያስያዘው ገንዘብ የማይመለስለት ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ለእያንዳንዱ ኩንታል የመጋዘን ኪራይ ብር 0.5 ይከፍላል።
9. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም። እንዲሁም ተጫራቹ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ እንጂ በከፊል መጫረት አይችልም።
10. ጨረታውን ያሸነፈ አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ ጠቅላላውን ዋጋ 10% የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችል።
11. ዩኒየኑ እህሉ ሽያጭ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም ከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0913277160 /0112363399 ይጠቀሙ።
አምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒዬን
