Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን የህዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ ምግብ ነክ፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

የተተቀዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 05/2018

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የህዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ ምግብ ነክ፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፤ ከሰዓት ከ7:00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  4. ማንኛውም የሐራጅ ጨረታ ተጫራቾች ለቦሎቄ እና ለእርግብ አተር ለእያንዳንዱ ኮድ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ግልፅ ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ይካሄዳል፡፡ የሃራጅ ጨረታው የግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ ይጀመራል፡፡ ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል።
  6. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
  9. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  11. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
  12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፣ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል፡፡
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-0462125396

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender