Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
  • Address Lagar, Ras Mekonen Ave, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-551 24 00
  • Websitehttps://eic-et.com/branches/
  • Deadline20 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security10,000.00
  • opening date2025-08-20 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ ለገሃር አካባቢ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሕንፃ ምድር ወለል ላይ የሚገኘውን ፣ በደቡብ ዲስትሪክት (መስቀል አደባባይ ላይ የሚገኘው ልዩ ስሙ በአንበሳ ሕንፃ) ስድስተኛ ፎቅ ላይ እና ልደታ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 41 አንደኛ ፎቅ ያሉ ባዶ ክፍሎች ለንግድ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)


 

የቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁ ኢአጽ/ግንአዳ/020/2017

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ ለገሃር አካባቢ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሕንፃ ምድር ወለል ላይ የሚገኘውን ፣ በደቡብ ዲስትሪክት (መስቀል አደባባይ ላይ የሚገኘው ልዩ ስሙ በአንበሳ ሕንፃ) ስድስተኛ ፎቅ ላይ እና ልደታ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 41 አንደኛ ፎቅ ያሉ ባዶ ክፍሎች ለንግድ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. ድርጅታችን ለኪራይ ያቀረባቸውን ክፍሎች በጨረታ መወዳደር / መሣተፍ የሚፈልግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 9፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ክፍል በኢትዮጵያ መድን ድርጅት (Ethiopian Insurance Corporation) ስም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ወይም ለዘጠና ቀናት በሚቆይ ቅድመ ሁኔታን ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ማለትም ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5512400 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

 

Save Tender