የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነቀምት ቅ/ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነቀምት ቅ/ፅ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢስስ/ግጨ/ነቀ/001/2018
መ/ቤታችን በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት መግለጫ |
የጨረታ ሠነዱ መግዥያ ዋና (የማይመለስ) |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር |
|
1 |
የቢሮ ኪራይ ጨረታ ለሶስት ዓመት የሚቆይ |
300.00 |
5,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነቀምት ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት 300 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ ታክስ ከሊራንስ ሰርተፊኬት/ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነቀምት ቅ/ፅ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ከፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል፡፡
- ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ነሀሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8:30 ሰዓት በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነቀምት ቅ/ፅ/ቤት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነቀምት ቅ/ፅ/ቤት
ስልክ ቁጥር:- 057-6-61-13-45/09-16-82-23-12
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነቀምት ቅ/ፅ/ቤት
