Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉጂ ዞን በአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ጀነሬተሮች፣ የግብርና ግብዓቶች እና መገልገያ እቃዎች፣ የሞተር ሳይክል፣ የኤሌትሮኒክስ እቃዎች፣ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ እቃዎችና የግንባታ እቃዎች፣ የትምህርት መሳሪያ እና የተለያዩ ሕትመቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉጂ ዞን የአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉጂ ዞን በአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ፣ ጀነሬተሮች፣ የግብርና ግብዓቶች እና መገልገያ እቃዎች፣ የሞተር ሳይክል፣ የኤሌትሮኒክስ እቃዎች፣ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ እቃዎችና የግንባታ እቃዎች፣ የትምህርት መሳሪያ እና የተለያዩ ሕትመቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት አቅራቢዎች ኤጀንሲ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ TIN number ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  4. በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 6፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት 7፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ 2% በኢትዮጵያ ውስጥ እውቅና ባላቸው ባንኮች በተረጋገጠ ኦርጅናል ሲፒኦ ወይም በካሽ ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማስገባት አለባቸው፤
  7. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀን የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ) በመክፈል ሰነዱን ከአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫት በመጨመር በገዙት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በግልጽ በመሙላት እንዲሁም በመጨረሻ ስም፣ ፈርማ እና የድርጅቱን ማሕተም በማኖር ኮፒና ኦርጅናሉን በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በመለየት ፖስታው ላይ በግልጽ መለየት አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ የድጋፍ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- 09 11 94 96 22 ወይም 0911 25 13 08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉጂ ዞን የአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender