በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ መ/ቤቶች የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ መ/ቤቶች የሚውል
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ
- የጽህፈት መሳሪያዎችና ሌሎች የቢሮ እቃዎች
- የጽዳት እቃዎች
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ፈርኒቸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ጨረታው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለ2018 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ስለመሳተፍ የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ ስራ ዘርፍ ትክከለኛ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ የሚውል ብር 10000 /አሥር ሺህ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከ2፡30 እስከ 11፡30 የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም 4:30 በቢሮ ቁጥር 10 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ5:00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ጽፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈዉን እቃ እስከ ኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ በማምጣት ማስረከብ አለበት።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሃሳቤን ቀይሪያለሁ ማለት አይቻልም።
- አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% /ፐርሰንት/ የውል ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጨረታ የሚከፈተው የበዓል ቀን ላይ ከዋለ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913311830 / 0916012874
የኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
