Tender Detail

Tender Details


በምዕራብ ወለጋ ዞን የግምቢ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ልዩ ልዩ የጽህፈት ማሣሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ትናንሽ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የምዕራብ ወለጋ ዞን የግምቢ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በምዕራብ ወለጋ ዞን የግምቢ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ልዩ ልዩ የጽህፈት ማሣሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ትናንሽ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተወዳዳሪዎችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ሀ/ የጨረታ መስፈርት

  1. ጥራት ያለው ዕቃ ለማቅረብ የሚችልና በንግድ ዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የ2017/ 2018 ንግድ ፍቃድ ያሳደሰ፡፡
  2. የግብር /TAX/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (TIN) እና ተጨማሪ የእሴት ታክስ የ(VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ፡፡
  3. ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ለተሸናፊዎች ይህ ማስያዣ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ ከሸነፉበት ጠቅላላው ዋጋ 10% ለውል ስምምነት በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚችልና 2% የሽያጭ ግብር ታክስ (TOT)መከፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግምቢ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማን በማድረግ በማሸግ የተጠየቁትን መስፈርት ዋና እና ኮፒውን በተለያየ በታሸገው ፖስታ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. ተወዳዳሪ በስሕተት ኦርጅናልና ኮፒውን በስህተት ቢቀያየር (misplacement) ከሆነ ተቀባይነት የለውም።
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቹን ግምቢ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በማቅረብ ለዚው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በ15ኛው ቀናት ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው የጨረታው መስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በ15ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የተወዳዳሪዎች መገኘት ወይም አለመገኘት ጨረታውን አያደናቅፍም፡፡
  10. የጨረታው አሸናፍዎች ያሸነፉበትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የቀረበው ዕቃ ጥራት ከሌለውና ያልተጠየቀ ዕቃ ከሆነ አቅራቢው ድርጅት ዕቃው የመመለስና መልሶ ጥራት ባለው የመተካት ግዴታ አለበት፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊዎች ፖልስቴር ጨርቅና ቴትሮን 6000 ጨርቅ በቀራበው ናሙና መሠረት የምንረከብና ቱታና የተለያዩ ጫማዎችንና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በባለሙያ ታይቶ ኦርጅናል መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ የምንረከብ ይሆናል፡፡
  12. በሁሉም ዕቃዎች ውድድሩ የሚካሄደው በያንዳንንዱ ነጣላ ዋጋ ይሆናል፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ወጭ እስከ ግምቢ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. የሞሉትን ዋጋ ከ (VAT) በፊት ወይም በኋላ መሆኑን መግለጽ አለበት፡፡ ካልሆነ ተቀባይነት አይኖርም።

ማሳሰቢያ

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የምዕራብ ወለጋ ዞን የግምቢ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

 

Save Tender