የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ መገልገያና ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ መገልገያና ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ምድብ 1 አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች
- ምድብ 2 የጽዳት ዕቃዎች
- ምድብ 3 የተለያዩ ሰነዶች ህትመት
- ምድብ 4 ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ዕቃዎች
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN No) ያላቸው
- የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለምድብ 1 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ፣ ለምድብ 2፡ ብር 35,000.00 (ሰላሳ አምስት ሺህ) ፣ ለምድብ 3 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) እና ለምድብ 4፡ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 21/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ቀን 21/12/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለምድብ 1 ፣ 2 እና 4 ናሙና የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ለምድብ 3 ድርጅቱ ናሙና ያቀርባል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር 0115525405/0115513288
ፖ.ሳ.ቁ 3375 አ.አ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
