Tender Detail

Tender Details

  • Company SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5 51 91 00
  • Websitehttps://www.filwuha.gov.et/
  • Deadline15 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-08-15 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Textile, Garment & Leather

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ ዕቃ ግዥ /አገልግሎት/ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ ዕቃ ግዥ /አገልግሎት/ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።  በዚህም፡-

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/ የአገልግሎት ግዥ

ሎት 1 የሥጋ አቅርቦት ግዥ

ሎት 2 የሠራተኛ የደንብ ልብስ ግዥ

  • ጃኬት
  • የዝናብ ልብስ
  • ቦቲ ጫማ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

  1. ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው ፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም።  ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
  7. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎች ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
  8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
  9.  ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች በምትጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሠረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  11. የጨረታ ሂደቱ ለሎት 1 የቴክኒክ ግምገማ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን ለሎት 2 ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሰነድ ግምገማና የናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ግን ቴክኒካል ግምገማ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ እና ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹን በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/011 5 15 73 37

 

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender