በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በማሻ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውል የጽህፈት መሳሪያዎች እና የቢሮ ውበትና ጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ /ሕ/ክ/መንግስት ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በማሻ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውል
- የጽህፈት መሳሪያዎች
- የቢሮ ውበትና ጽዳት እቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይጋብዛል፡፡
- በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱ ዕቃዎች ቀጥታ ግንኙነትና አግባብነት ያላቸው የ2018 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ ያሳደሱ ፣ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ አስመዝገባቸው የምስክር ወረቀት እና የቫት /የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደርባቸው ተራ ቁጥር 1 እና 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አሥር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ከእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ማሻ ከተማ ገ/ቅ/ባ/ስ/ጽ/ቤት ቢሮ ገንዘቡን በመክፈል ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ማሻ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ 1 ኦርጂናል እና 2 ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ማሻ ከተማ /ፋ/ኢ/ ጽ/ቤት የግዥ ን/አስ/ር ሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ በዚህ ጨረታ አገ/ት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን የመንግሥት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በማሻ ከተማ ፋ/ኢ/ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
- ውል እንዲገባ ከተጻፈበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ዕቃዎችን በራሱ መጋዝን ማዘጋጀት ማቅረብ/ አለበት።
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለበት።
- የሚቀርቡ እቃዎች ጥራት ያላቸውና በተሰጣቸው እስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ 0475580530፣ 0474522817 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በደ/ም/ኢ/ክ/መንግስት ማሻ ከተማ /ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
