Tender Detail

Tender Details


የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ የሚውል ጥራጥሬ፣ ብዕር እህሎች ፣ እህልን ለማስፈጨት ፣ ፍራፍሬ ፣ ማገዶ (ግንድላ) እና ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች እንዲሁም ለእንስሳት መኖ እና የዶሮዎች ምግብ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ የሚውል ጥራጥሬ፣ ብፅር እህሎች ፣ እህልን ለማስፈጨት ፣ ፍራፍሬ ፣ ማገዶ (ግንድላ) እና ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች እንዲሁም ለእንስሳት መኖ እና የዶሮዎች ምግብ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችሁዋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት በንግድ ዘርፍ ላይ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው ከምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ከፎቅ ቁጥር 1 ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ክፍል ቁጥር 13 መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ካለፉት ዓመታት በአቅራቢነት ችግር ያልፈጠሩ ጥሩ የአቅራቢነት ባህሪይ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond (CPO) 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ምግብ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት።
  6. ተጫራቾች የምግቡን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን “Specification” ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋውን በመሙላት ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማሰፈር ማህተም ማድረግ ግዴታ አለባቸው።
  7. የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናል ቴከኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖሰታ እና ኮፒውን ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ ትልቁ ፖስታ በ15ኛው ቀን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ10፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ከሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
  9. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር የተሰጠውን መመሪያ (መስፈርቶች) በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተያይዞ የቀረበ መመሪያ መከተል አለባቸው።
  10. የጨረታው ሣጥን ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  11. የጨረታ አሸነፊ ተጫራቾች ምግብም ሆነ ሌሎች ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ከውል ሰጪው መ/ቤት ጋር በሚያደረገው የውል ስምምነት መሠረት ነቀምቴ በሚገኘው በወል ሰጭው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
  12. መ/ቤታችን በሚያወዳድረው ጠቅላላ የዋጋ ብዛት ላይ እንደየአስፈላጊነቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
  13. ተጫራቾች ምግብ አሸንፊው ለማቅረብ ሲዋዋሉ ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  14. ተጫራቾች ጨረታውን አሸነፊ መሆናቸው ከተገለጸ ከአምስት ቀን በኋላ በውል ሰጪው መ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት የመፈፀም ግደታ አለባቸው።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስልክ 057-6-60-22-07 / 057-6-61-34-10 / 057-6-60‐13-02

 

የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

 

Save Tender