Tender Detail

Tender Details


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ208 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ208 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽሕፈት መሣሪያዎች /ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ 2%

ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ /2%/

ሎት 3 የደንብ ልብስ ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ /2%/

ሎት 4 የህትመት ሥራዎች 10,000 /አስር ሺ ብር/

ሎት 5 የመስተንግዶ አገልግሎት 10,000 /አስር ሺ ብር/

ሎት 6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት 10,000 /አስር ሺ ብር/

ሎት 7 የጉልበት ሥራ አገልግሎት 10,000 /አስር ሺ ብር/

ሎት 8 የሞንታርቦ ኪራይ እና የአዳራሽ ዲኮር አገልግሎት ለእያንዳንዱ አገልግሎት 10,000 /አስር ሺ ብር/

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ሲፒኦ ማሠራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  1. የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የገበሩ
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. በመንግሥት ግዥ የአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ለተቀመጡት ዝርዝሮች ያስገቡትን የዕቃ ዋጋ 2% እና ሌሎች ለተዘረዘሩ አገልግሎቶች በየሎቱ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ሲፒኦ ማሠራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ልግሎቶች ቀናት የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚሠሩ ከሥራና ክህሎት ጽ/ቤት የትብብር ደብዳቤ በማምጣት በተፈቀደላቸው ዘርፍ ላይ ብቻ ያለክፍያ የጨረታ ሰነድ መውሰድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሳያሲዙ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ከሚያመርቱት ምርት ውጪ በሆኑ ዕቃዎች ላይ እንደማንኛውም ነጋዴ የጨረታ ሰነድ መግዛትና ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  8. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ፣ ስርዝ ድልዝ የሌለው ዋጋ መሙላትና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ከሚያስገቡት ዶክመንት ጋር በማያያዝ ተመላሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ናሙና በሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ እስከሚቆይበት ጊዜ ብቻ ናሙናውን ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፧

ማሳሰቢያ፡- ለናሙና ማስቀመጫ በቂ ቦታ ስለሌለን የጨረታው ሂደት እንደተጠናቀቀ በ1ወር ውስጥ ያቀረባችሁትን ናሙና እንድትረከቡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶለሚፈጠረው የንብረት ብክነት እና ብልሽት ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ፡- አ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ቦታ ተክለኃይማኖት በርበሬ በረንዳ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት

 

Save Tender