Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111-57-47-99
  • Website
  • Deadline01 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security5000.00
  • opening date2025-08-02 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent , Land, House, Building And Warehouse Rent

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆኑትን ለንግድ የሚሆኑ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት


 

የንግድ ቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆኑትን ለንግድ የሚሆኑ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
  2. የቤቶቹ አድራሻ- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር መጋዘን ቁጥር 10 እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የሚኘውን የላሜራ ቤት፤
  3. መንግሥታዊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ተወዳዳሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ሆኖ ከሚገለገልበት ደብር የድጋፍ ደብዳቤና የአባልነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችል፤
  4. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ቤቱን ከተረከበ በኋላ የውሃና የመብራት ፍጆታ ራሱ ይከፍላል።
  5. ድርጅቱ ለኪራይ ያቀረበውን መጋዘን እና የላሜራ ቤት በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ክፍሉን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ ገዝቶ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፡ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች በጥቅልም ሆነ በተናጥል ሲወዳደሩ የሚጫረቱበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000.00 በማስያዝ የጨረታ ማስበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ቤቶቹን ከፋፍሎ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
  9. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ዝርዝር መመሪያ ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

ለበለጠ መረጃ

በስ.ቁ. 0911-78-86-98 ወይም

በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ

 

Save Tender