የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ተኝተውና ተመላልሰው ለሚታከሙ ህሙማን የሚውል መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችንና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎችን፣ ለሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ለተኝቶ ታካሚዎችና ለህክምና ተማሪዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆኑ ጥራጥሬዎች፣ አትክልት፣ ዳቦ፣ እንጀራ፣ የህንፃ ጥገና ቁሳቁሶች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ለመግዛት እና የመኪናዎች ጥገና ስራ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድረው ለማስጠገን ይፈልጋል።
Yirgalem Medical college (የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ተኝተውና ተመላልሰው ለሚታከሙ ህሙማን የሚውል መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችንና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎችን፣ ለሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ለተኝቶ ታካሚዎችና ለህክምና ተማሪዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆኑ ጥራጥሬዎች፣ አትክልት፣ ዳቦ፣ እንጀራ፣ የህንፃ ጥገና ቁሳቁሶች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ለመግዛት እና የመኪናዎች ጥገና ስራ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድረው ለማስጠገን ይፈልጋል።
- ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ
- የጨረታ ማስከበሪያ የክፍያ ማዘዣ CPO ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ማስዝያዝ የሚችሉ
- በጨረታ ላይ ለመወዳደር የሚያስችል ማስረጃ ከገቢዎች ቢሮ የተሰጣቸውንና የታደሰ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃዳቸውን ተ.እ.ታ. የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክሜንቱን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ስራ ቀናት ውስጥ ይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ሁለት ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናሻል ኦርጂናል ሁለት ፋይናሻል ኮፒ ሰነድ እያንዳንዱን ፖስታዎች የድርጅቱን ማህተም ተደርጎና በሰም በማሸግ በአንድ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ በተጫራች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ እና ቁልቁል ተደምሮ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00/ስድስት ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰዓት/ ላይ በግልፅ ይከፈታል።
- የወቅቱ የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበው የዋጋ ትንታኔ መያዝ አለበት።
- አሰሪ መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ለተጨማሪ መረጃ ቁጥር 0909495415 እና 0911 708366 ይደውሉ።
የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ
