የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ2018 ዓ.ም ከመንግስት በተመደበ በጀት ለአንድ አመት የሚቆይ የማዕቀፍ እና የአንድ ጊዜ የህትመት አገልግሎቶች ግዥ ለመፈጸም በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/መ/ቁ መ/ኮ 01/2018
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ2018 ዓ.ም ከመንግስት በተመደበ በጀት ለአንድ አመት የሚቆይ የማዕቀፍ እና የአንድ ጊዜ የህትመት አገልግሎቶች ግዥ ለመፈጸም በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና በመንግስት የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ጨረታው እስከ የሚታሸግበት እለትና ሰአት ቀደም ብሎ የጨረታ ሠነዱን ከቢሮው የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ቀርበው የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች አስፈላጊውን ዋጋ በግልጽ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በመግለጽ ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- የጨረታ ሳጥኑ ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በሥራ ሂደቱ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ብር 8,000 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ፣ በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ ዋስትና ፣በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ሲፒኦ ከነዚህ አማራጮች በአንዱ በመጠቀም ለብቻው በአንድ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የስልክ ቁጥር 0251-11-60-61
ሞባይል፡- 0948597011
ፋክስ ቁጥር 0251114972
የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
