Tender Detail

Tender Details


መ/ቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አካባቢያቸው ባሉ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ሲቪል ኢንጂነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር በጃክ ሀመር እና ሮለር የኪራይ አገልግሎት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/ 01/18

 

መ/ቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አካባቢያቸው ባሉ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ሲቪል ኢንጂነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር በጃክ ሀመር እና ሮለር የኪራይ አገልግሎት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም:-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ የመንግሥት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተመሳሳይ ሠዓት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዘንድ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ /CPO/ ለአንድ ማሽን ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ በማሠራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም

ስልክ ቁጥር 0113659932

ወልቂጤ ኢትዮጵያ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን

 

Save Tender