Tender Detail

Tender Details


የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለአንደኛ ዙር የወጣ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ እና ውል መፈፀም ይፈልጋል።

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ


 

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለአንደኛ ዙር የወጣ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ እና ውል መፈፀም ይፈልጋል፤ የዚህም ጨረታ የገንዘብ ምንጭ የመንግስት ግምጃ ቤት እና የውስጥ ገቢ ነው፡፡

በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-

  • ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከአደራጃችሁ ተቋም የአምራችነት ደብዳቤ በማምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 411 የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ ሰነዱ ውስጥ በሚገኝ የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር መሰረት ከነቫቱ ሞልተው ያስገባሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር
  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ የጽሕፈት እቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 0.2 %) 4000 ብር ፤
  • ሎት2 ቋሚ እቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 0.2 %) 10800 ብር፤
  • ሎት 3 የተለያዩ ህትመቶች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 0.2 %) 2400 ብር፣
  • ሎት 4 የተለያዩ የጥገና ስራዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 0.2% 5600)
  • ሎት 5 የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ስፌት (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 0.2%) 3000 ብር፤
  • ሎት 6 የፅዳት እቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 0.2%) 3000 ብር፣
  • ሎት 7 የተለያዩ ለጥገና ሥራ የሚያገለግሉ ዕቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 0.2%) 1200 ብር
  • ሎት 8 የሰው የሕክምና መድኃኒት እና የሕክምና ዕቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 0.3 %) 47247
  • ሎት 9 የተለያዩ የካፌ አገልግሎቶች 1000

የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ በጤና ጣቢያው ስም ተሰርቶ ሙሉ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች ተሞልተው ሰነዱ ተፈርሞበትና የድርጅቱ ማህተም ተደረጎበት ይመለሳል፤ ለጥቃቅን ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ ከአደራጃችሁ ተቋም ማምጣት ይኖርባችኋል ፡፡ ሙሉ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች ተሞልተው ኮፒ ተደርጎ ከዋናው ሰነድ ጋር ሲፒኦ በማድረግ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ ተጫራቾች ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዕለቱ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ተዘግቶ 3፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል በማንኛውም ምክንያት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ወድቅ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ጥብቅ ማሳሰቢያ፡- የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን ዋጋ ሞልታችሁ የምታስገቡት የመድኃኒት ዋጋ ከሞላችሁበት ጋር ሳይሆን የሕክምና እቃዎችን የሞላችሁበትን ፖስታውን ከተቋሙ የምትወስዱትን የጥራት መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና ስለማሽኑ የሚገልፅ ካታሎግ አንድ ላይ በማድረግ ለብቻው ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡

አድራሻ፡- ከኮካ አደባባይ ወደመሣለሚያ ወይም ከመሣለሚያ ወደ ኮካ አደባባይ በሚሄደው ዋና መንገድ ሲሄዱ የቀድሞ 24 ቀበሌ መዝናኛ ክበብ ፊት ለፊት ባለው ዳገታማ መንገድ 200 ሜትር እንደሄዱ በሚታየው ባለ አራት ፎቅ ሕንፃ ላይ ያገኙናል፡፡

ተጨማሪ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 011 827-56-08 ወይም 011 827-90-60/

ማሳሰቢያ፡-

  • ማንኛውም ተጫራች ስፔስፊኬሽን /የጥራት ልዩ መግለጫ/ ከተገለፀላቸው ዕቃዎች ውጪ ለተወዳደሩበት ማንኛውም ዕቃዎች ናሙና እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ሳይከፈት ተመላሽ ይደረጋል ማለትም ለውድድር አይቀርብም፡፡
  • በልብስ ስፌት አገልግሎት ሥራ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የስፌት ዓይነት የተሰፋ ልብስ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡

የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ሁሉ ከቫት ጋራ የተሰላ /ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን ይኖርበታል ከቫት ጋራ ያልተሰላ /ተጨማሪ እሴት ታክስን/ ያላከተተ ከሆነ ለአሠራራችን አመቺ ስለማይሆን ለውድድር አናቀርበውም፡፡

 

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ

 

Save Tender