Tender Detail

Tender Details

  • Company Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)
  • Address ዋና መ/ቤት የድሮ መርከብ ሕንፃ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አጠገብ ያለው ሕንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115539535
  • Websitehttps://www.fhc.gov.et/en#New
  • Deadline11 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security25000.00
  • opening date2025-08-11 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር የሚገኙ የንግድ ድርጅት ቤቶችን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)


 

የ13ኛ ዙር የንግድ/ድርጅት ቤቶች ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/02/11/2017

 

  1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር የሚገኙ የንግድ ድርጅት ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/02/11/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
  2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የንግድ ድርጀት ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ የኪራይ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓት ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው።
  4. ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከሀምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነዱን በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢ አደራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ወይም ነሐሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት 9፡30 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሀያ አምስት ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 09-64-60-27-33 ወይም 09-10-48-59-48 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ. PO. Box 299

ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46-46

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender