የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱት የተለያዩ አቅርቦቶች /ስራዎች በመስኩ ከተሠማሩ ድርጅቶች ጋር ውል በማሰር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀምና ስራውን ለማሠራት ይፈልጋል።
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱት የተለያዩ አቅርቦቶች /ስራዎች በመስኩ ከተሠማሩ ድርጅቶች ጋር ውል በማሰር በግልፅ ጨረታ አወዳሮ ግዥ ለመፈፀምና ስራውን ለማሠራት ይፈልጋል።
- ደረጃውን የጠበቀ የጤፍ ዱቄት
- አትክልትና ፍራፍሬ
- የስጋ አቅርቦ
- የምግብ ቅቤ እና የማር
- የዶሮ እና የእንቁላል አቅርቦ
- የጥራጥሬ እና የታሸጉ የምግብ ሸቀጦች
- ዓሣ አቅርቦት
በዚህ መሠረት ማንኛውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ አካል በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- በመስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የ2013 ዓ/ም ግብር የከፈሉ፤
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ፤
- የግብር መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው ሆነው የምስክር ወረቀት የተሰጣቸውና ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነዱን በመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ገንዘብ ያዥ ድረስ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 11፡00 ሰዓት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናውንና አንድ ኮፒ በመያዝ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ መከፈቻ ቀን ለእያንዳንዱ ሠነድ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በክበቡ ግዥ ክፍል ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሠነዱ ስርዝ ድልዝ ቢኖረው ባይፈረምና በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከጨረታው ይሰረዛል።
ማሳሰቢያ፡- ክበቡ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ጦር ኃይሎች አካባቢ
ስልክ ቁጥር:- 0113-71 73 17/0113-71 58 50
የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ
