Tender Detail

Tender Details

  • Company የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113301548
  • Website
  • Deadline30 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-30 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Vehicle tire

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በጥቅል ግዥ ለመፈፀም በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው በኦንላይን የተመዘገቡ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር-001/2018

 

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በጥቅል ግዥ ለመፈፀም በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው በኦንላይን የተመዘገቡ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች

ሎት-2 የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች

ሎት-3 የተለያዩ የፎቶ ኮፒ እና የኮምፒተር ቀለሞች

ሎት-4 የተሽከርካሪ ጎማ

በዚህም መሰረት፡- ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የግብር ከፋይመለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በኦንላይን የተመዘገቡ በe-GP/ (electronic government procuurment) ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ፤ CPO ለሎት-1 /50,000 ለሎት-2/ 50,000 ሎት-3 /50,000 እና ለሎት- 4 /50,000 በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና/ስራ/ሂደት ክፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ተወዳዳሪ የሚለየው ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዱ ነጠላ እቃ ባቀረቡት ዋጋ መሰረት የቀረበ አነስተኛ ዋጋ ወይም በጥቅል ሎት የተሻለውን የጨረታ አሸናፊ የመለየት ስራ ሊሰራ ይችላል ፡፡
  • ማሳሰቢያ፡- ፅ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  • በጨረታው መከፈቻ ቀንና ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  • መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ሞልቶ መወዳደር አይቻልም፡፡
  • የጨረታ ማስታወቂያውንና የጨረታ ሰነዱ የሚጠይቀውን ዝቅተኛ መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ወይም በኦንላይን ያልተመዘገቡ ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
  • የጨረታውን መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሄራዊ የህዝብ በዓል ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡

ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113301548/0911921780/ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender