Tender Detail

Tender Details


በልደታ ክ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ መድሐኒት እና የህክምና እቃዎች፤ የጥገና እቃዎች አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች የፅዳት እቃ፤ ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች የህትመት ስራዎች እና ደንብ ልብስ እና የሰራተኛ ክበብ ወይም በካፌ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በልደታ ክ/ከተማ የጄነራስ ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ


 

የ2018 ዓ.ም በጀት አመት የአንደኛ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በልደታ ክ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ መድሐኒት እና የህክምና እቃዎች፤ የጥገና እቃዎች አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች የፅዳት እቃ፤ ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች የህትመት ስራዎች እና ደንብ ልብስ እና የሰራተኛ ክበብ ወይም በካፌ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በዚህም መሰረት፡-

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የመስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በጤና ጣቢያዉ እረዳት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 40 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት1 መድሐኒትና ህክምና እቃ 215,000, ሎት2 የጥገና እቃ 15,999 ሎት 3 የፅህፈት እቃ 16,600, ሎት4 ህትመት ስራ 13,500 ሎት5 ደንብ ልብስ 16,000 ሎት6 የፅዳት እቃ 13,500 እና ሎት7 የቋሚ እቃ 21,000 እና ለሰራተኞች ክበብ ወይም ካፌ 30,000 በCPO/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡ የእቃ አይነት (ሳምፕል) ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ የሚያቀርቡትን እቃ ዋጋ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የግዥውን አይነት በኤንቬሎፑ ላይ በመጥቀስና ማኅተም በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጤና ጣቢያዉ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰእት ተዘግቶ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት የሚከፈት ሲሆን እለቱ በአል ቀን ከሆነ የሚቀጥለዉ የስራ ቀን ተጫራች አባለት በተገኙበት በጤና ጣቢያው አዳራሽ ይከፈታል።
  9. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ አሟልተዉ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም
  11. ጤና ጣቢያው የሚጫረተውን እቃ ብዛት እንደአስፈላጊነቱ በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች ላሸነፉት እቃ የአንድ አመት ዋስትና መስጠት አለባቸው፡፡
  12. ጤና ጣቢያዉ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ብስራተ ገብርኤል አደባባይ የኢ/መ/ፋ/ፊት ለፊት ልደታ ክ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118347566 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በልደታ ክ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender