የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚ/ር፣ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚ/ር እና የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ ልዩልዩ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ
ቁጥር PPS/NVP-6FBI/01/11/2017
የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚ/ር፣ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚ/ር እና የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የንብረቶች ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ በቴሌብር እና ሲቢኢ ብርን በመጠቀም የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒአ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
- አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 13 78 56 06 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት
አዲስ አበባ
