Tender Detail

Tender Details


የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ 04/11/2017 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ 04/11/2017 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት፤ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የጨረታ መስፈርቶች፡-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 04/1/2017 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 ሰዓት እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 ሰዓት የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5በመቶ አንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ ኣሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

የጨረታው ቦታ

የጨረታው ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

ግልጽ ጨረታና በሐራጅ

ጫማዎች አልባሳትና  ኮስሞቲክስ፤ የመኪና መለዋወጫ፤ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ ምግብ ነክ፤ የስፖርት እቃዎች፤ የእጅ ሰዓት፤ የመነጽር አሮጌ የመኪና ሞተሮች ኤሌክትሮድ አሉሚነም ፕሮፊይል፤ ረከቦት፤ የግንባታ እቃ፤ የወዳደቁ ፕላስቲኮች ጎማዎችና ቸርኬዎች ተሽከርካሪ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልጽ ጨረታ በ 04/11/2017 እስከ ጠዋቱ 3፡45 ለሐራጅ ጨረታ እስከ 4፡45

ለግልጽ ጨረታ 04/11/2017 እስከ ጠዋቱ 4፡00 ለሐራጅ ጨረታ 5፡00

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  2. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሎት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  3. ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።
  4. ከላይ በተቁ7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  5. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender