Tender Detail

Tender Details

  • Company የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address ሳሪስ ከነጋ ቦንገር ወደ ብሄረጽጌ በሚወስደው መንገድ በላብያጆ ገባ ብሎ ባለው የኮብልስቶን መንገድ ትንሽ ገባ እንዳሉ ወደቀኝ በመጀመሪያ መታጠፊያ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-66-43-15-54
  • Website
  • Deadline15 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-15 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Machinery

የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ንብረት የሆኑትን ያገለገሉ የስፌት ማሽኖችና የሽመና ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ንብረት የሆኑትን ያገለገሉ የስፌት ማሽኖችና የሽመና ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 28/10/2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 8/11/2017 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት 3፡00 እስከ 10:00 ሰዓት በመጨረሻው ቀን በ8/1/2017 እስከ ጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች መመልከት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ በብርሃን ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታ ግምገማ ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃዎች ዝርዝር ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፈደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ (ፖስታ) በድርጅቱ የጨረታ ሳጥን ውስጥ 8/11/2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ አድርገው በ5 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ያስገቡት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) እየከፈሉ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8/11/2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ ፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 5፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ሊያገኙ ይችላሉ።
  9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-66-43-15-54 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ሳሪስ ከነጋ ቦንገር ወደ ብሄረጽጌ በሚወስደው መንገድ በላብያጆ ገባ ብሎ ባለው የኮብልስቶን መንገድ ትንሽ ገባ እንዳሉ ወደቀኝ በመጀመሪያው መታጠፊያ።

 

የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት

 

Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE