Tender Detail

Tender Details

  • Company የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል
  • Address አራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 7 ከስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1 261365
  • Website
  • Deadline10 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-11 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

የአራት ኪሎ ስፖርት፤ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል የምግብ ግብዓቶች ለአንድ ዓመት በአቅራቢነት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል


 

የምግብ ግብዓቶች ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/2017 ዓ.ም.

 

1. የምግብ ግብዓቶች ለአንድ ዓመት በአቅራቢነት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የተጫራቾች መመሪያ በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች -

  1. ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራቾች የምግብ ግብዓት አቅራቢነት በስራ መስክ፤ የዘመኑን ግብር፣ ለመክፈላቸውን ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No. ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል ።
  4. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖር አይፈለግም ፡፡ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉና ከተዋዋሉ በኋላ ያሸነፉበትን የምግብ ገብዓት በተሰጠው ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆነ በውሉ መሰረት በህግ ይጠየቃል፡፡ ለምግብ ግብዓት ባሸነፈው ለአንድ ዓመት የዋጋ ጭማሪ ካለ ለሶስት ወር ከአቀረቡ በኋላ ከአገሪቱ ገበያ ዋጋ ጋር ግምት ውስጥ ገብቶ ተነፃፅሮ ይሻሻላል፡፡
  6. ተጫራቾች መ/ቤቱ ያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የምግብ ዝርዝር ያየዘው የአንዱ ዋጋ ከነቫት መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ዋጋ ሲሞላ የተጫራቹ ሙሉ ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም ያረፈበት፣ አድራሻ፣ክፍለ ከተማ፣ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸውን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች መ/ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከአራት ኪሎ ስፖ/ትም/ስል/ማዕከል የፋይ/ ግዥ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት በ400 ብር ብቻ /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑንን እየገለፅን፣ ጨረታውን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ የሚያበቃና ሳጥኑም ታሽጎ በማግስቱ የስራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የስራ ቀናት ካልሆነ ደግሞ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በማዕከሉ አዳራሽ ቁጥር 10 በግልፅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ድርጅቱን የሚገልፅ ህጋዊ መታወቂያና ውክልናን የሚገልፅ ደብዳቤ በመያዝ ጨረታው ሲከፈት መከታተል ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር / የስራ ቀናት ውስጥ በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ (copy) እና አያይዘው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይ/ግዥ/ንብ/ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 8 ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ለምግብ ግብዓት የጨረታ ሰነድ ከማስገባታቸው በፊት ናሙና የሚጠይቅበት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፤ ካላቀረቡ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡ ጨረታው በግልፅ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም መረጃ /ዶክመንት/ ማቅረብ አይቻልም ፡፡
  12. ለአሸናፊዎቹ ክፍያ የሚፈጸመው የተጠየቀውን የምግብ ግብዓት በተጠየቀውና ባሸነፈው ናሙና መሰረት ሙሉ በሙሉ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ካደረገ በኋላ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የምግብ ግብዓት በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
  15. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገልግል የመጫረቻ ዋጋ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ሰነድ ኦሪጅናል ፖስታ ውስጥ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  16. ተጫራቾች ከአሸናፉ በኃላ የውል ዋስትና 10% ሲፒኦ (CPO) ብቻ ከባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል፡፡

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 8 ከሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት

 

የአራት ኪሎ ስፖርት፤ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል

 

Save Tender