የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች/ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አአከአአድ/ሱኪ/ግጨቁ/02/2017
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች/ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
- ተጫራቹ የህጋዊ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ቦታ (ኮድ) በታሸገ ኤንቨሎፕ (ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ) ማቅረብ አለባቸው።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 10% በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች/ ግለሰቦች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ እስከ ስድስት ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8-01 በመምጣት መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሆኖ በዕለቱ (በአስራ አምስተኛው ቀን) በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን ዕሁድ/ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-6-66-33-67 መደወል ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ የድርጅቱን ማህበራዊ ድረ-ገፆች ይጎብኙ፦
Facebook:- https://www.facebook.com/citybus2015
Telegram:- https://t.me/citybus
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
