በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ ባንዲራና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባንዲራ ከነስታንዱ፤ ፍላሽ ዲስክ፣ ቀበቶ፣ የኪስ ቦርሣ እና የላፕቶፕ መያዣ ቦርሣ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/2Re-08/2017
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ ባንዲራና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባንዲራ ከነስታንዱ፤ ፍላሽ ዲስክ፣ ቀበቶ፣ የኪስ ቦርሣ እና የላፕቶፕ መያዣ ቦርሣ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባና የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2017 ዓ/ም) ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የተጠቀሱትን ኮፒ ሰነዶች በመያዝ የማይመለስ ብር 100.00 ከቫት በፊት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ 011 442 0216
ፋክስ 011 442 0688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
