Tender Detail

Tender Details


በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በወረዳ 10 ቢሪሞ ሜዳ የሚገኘውን G+1 ለንግድ ቤት የሚሆኑ የተለያዩ ሱቆችና ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የቢሪሞ ሱቅ ቁ.1 እና የቢሪሞ ሰቅ ቁ.2 አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SM 03/2017

 

በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በወረዳ 10 ቢሪሞ ሜዳ የሚገኘውን G+1 ለንግድ ቤት የሚሆኑ የተለያዩ ሱቆችና ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የቢሪሞ ሱቅ ቁ.1 እና የቢሪሞ ሰቅ ቁ.2 አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል። ቤቶቹ የምድር ቤትና G+1 ያለው ሲሆን፣ አጠቃላይ ብዛቱ 21 ሱቆች ሲሆን ፣ የተሟላ ሽንት ቤት፣ ውኃና መብራት እንዲሁም ጥበቃ ያለው መሆኑን እናሳውቃለን። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. የታደሰ የቀበሌ /የነዋሪነት/ መታወቂያ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን የተገዛበት ወይም የተከፈለበት ገቢ ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አብሮ ከጨረታ ሰነዱ ጋር /መያያዝ/ ማስገባት ይኖርበታል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ‹‹በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ምክር ቤት» ስም በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሠዓት በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 አዲሱ የልደታ ክ/ከተማ ህንፃ ላይ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ፋይናንስ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. የተሞላው ዋጋ በተጫራቾቹ በግልጽ ጽሁፍ መቀመጥ እና መፈረም አለበት።
  6. በተጫራቹ የተሞላው ዋጋ በግልጽ ፅሁፍ መቀመጥ እና መፈረም አለበት።
  7. አንድ ተጫራች መጫረት የሚችለው ለአንድ (1) ሱቅ ብቻ ነው። ይህን ተላልፎ የተገኘ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
  8. አሸናፊ አካላት ሱቆቹ ለመጠጥና ከመጠጥ ጋር የተያያዙ ንግዶችን ለብረታ ብረት ብየዳ ስራ፣ ለቁማር (ቤቲንግ)፣ ለጫትና ሲጋራ እንዲሁም አካባቢ በድምጽ የሚረብሹ ነገሮች መጠቀም ክልክል ነው።
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ የስራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ካልሆ ግን በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0118722106 ከልደታ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ/ በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502

 

በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender