በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ያገለገሉ የግንባታ ግብዓቶች (ቆርቆሮ፣ አልሙኒየም በር እና ብረቶች) እና አሮጌ የመኪና ጎማዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
ያገለገሉ ልዩ ልዩ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር OFWE/MM-003/2017
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ያገለገሉ የግንባታ ግብዓቶች (ቆርቆሮ፣ አልሙኒየም በር እና ብረቶች) እና አሮጌ የመኪና ጎማዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሠነዶችን ለእያንዳንዳቸው መደብ (ሎት) የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ ለማየት ከፈለጉ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-11:00 ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል።
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፋትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ምድብ (ሎት) ዋጋ (5%) አምስት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid bond) በባንክ ክፍያ ማዛዣ (CPO) ኣሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በሚል በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111240249 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
