Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ
  • Address ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር እልፍ ብሎ በቀድሞው የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና መ/ቤት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-01-95-69-26
  • Website
  • Deadline23 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-23 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent , Cargo Vehicle , Transportation Service And Cargo

የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ ከሚድሮክ ኢትዮጵያ የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ ኑራኤራ እና መርቲ ጀጁ እርሻ ልማት (190 ኪ.ሜ ላይ) የሚገኘውን የአትክልትና ፍራፍሬ (ብርቱካን፣ ማንጎ እና የሙዝ) ምርቶችን ወደ አዲስ አበባ የሚያመጡ የመጫን ችሎታቸው ከ70 - 80 ኩንታል የሆኑና የስሪት ዘመናቸው እ.ኤ.አ ከ2015 ወዲህ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ


 

የጨረታ ማሰታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 01/2017 ዓ.ም

 

ዘርፋችን ከሚድሮክ ኢትዮጵያ የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ ኑራኤራ እና መርቲ ጀጁ እርሻ ልማት (190 ኪ.ሜ ላይ) የሚገኘውን የአትክልትና ፍራፍሬ (ብርቱካን፣ ማንጎ እና የሙዝ) ምርቶችን ወደ አዲስ አበባ የሚያመጡ የመጫን ችሎታቸው ከ70 - 80 ኩንታል የሆኑና የስሪት ዘመናቸው እ.ኤ.አ ከ2015 ወዲህ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /VAT/ ያላቸው፤
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 5% በዘርፉ ስም /CPO/ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ጨረታው እንዳበቃ /CPO/ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለሳል።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የሥራ ቀናት ድረስ የሚደመስስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይችልም፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ጨምረው መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማስታወቂያው ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በሰባተኛው ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ቀኑ እሁድ ውይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ወይም ግለሰብ ለንብረቱ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር-09-01-95-69-26 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ዋናው መ/ቤት ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር እልፍ ብሎ በቀድሞው የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና መ/ቤት

 

የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶች ንግድ ዘርፍ

 

Save Tender