በመከላከያ ስራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ያገለገለ የተለያዩ የስፌት ማሽኖች፤ ኮምፕረሰሮች፤ ብረታ ብረቶች እና የተለያዩ ጨርቃ ጨርቆችና አልባሳቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በመከላከያ ስራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ያገለገለ የተለያዩ የስፌት ማሽኖች፤ ኮምፕረሰሮች፤ ብረታ ብረቶች እና የተለያዩ ጨርቃ ጨርቆችና አልባሳቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ፡-
- ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የተግበረበት ንግድ ፈቃድ፡ ቫት ተመዝጋቢ ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታው መወዳደሪያ ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ሰነዶች ህጋዊ ንግድ ፈቃዶች እና ታክስ ከፋይ ሰነዶችን ይጨምራል እና ፋይናንሻል መግለጫ በፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዶቹ የድርጅታቸው ማህተምና የኃላፊው ፊርማ ያለበት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኮሚቴው ሰብሳቢ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን በ7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ8፡30 ሰዓት በኢንዱስትሪያችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጁትን ዕቃዎች በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ /አዳማ/ በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ።
- ኢንዱስትሪው የተሻሉ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ አዳማ ፍጥነት መንገድ የክፍያ በር መውጫ ከአዳማ ቆርቆሮ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ 500 ሜትር ላይ
በስልክ ቁጥር፡- 09-10-73-78-72/09-39-12-50-16
