Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116 18 61 25
  • Website
  • Deadline27 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-27 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Consumable Goods , Other Sales

የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኝ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የዕጣን ምርት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ


 

የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ

የዕጣን ምርት ሽያጭ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - ኢምዘደውአዘ/ግጨ/ሸ02/2017

 

የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኝ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የዕጣን ምርት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት) አዲስ አበባ በሚገኘው በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 እና የማይመለስ ብር 200,00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በCPO በኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል የጨረታው ዋጋ ለ 60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
  4. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። የዕጣን ምርት ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨምራል።
  5. ጨረታው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረበው የዕጣን ምርት መጫረት ይቻላል።
  7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  8. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስልክ 011 6 18 61 25  

 

የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ

 

Save Tender