Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሆሳዕና ቅ/ፅ/ቤት
  • Address ሆሳዕና ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0465552282
  • Website
  • Deadline24 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-24 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

መ/ቤታችን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሆሳዕና ቅ/ፅ/ቤት


 

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢስአ/ግጨ/ሆሳ/001/2017

 

መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ

የግዥው ዓይነት መግለጫ

የጨረታ ሠነዱ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ)

የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር

1

ለ2 ዓመት የሚቆይ ቢሮ ኪራይ ጨረታ

100.00

5,000.00

 

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሆሳዕና ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር በመምጣት 100 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት /TIN number/ እና በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ የታክስ ክሪላንስ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሆሳዕና ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
  5. ሠነዳቸውን አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በአዲሱ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
  6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሆሳዕና ቅ/ፅ/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 0465552282/ 0911015240/0913810613

 

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት

 

Save Tender