መ/ቤታችን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሐረር ቅ/ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢስአ/ግጨ/ሀረ/001/2017
መ/ቤታችን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት መግለጫ |
የጨረታ ሠነዱ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ) |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን |
|
1 |
የቢሮ ኪራይ ጨረታ |
100.00 |
5,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀረር ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር በመምጣት 100 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት /TIN number/ እና በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ የታክስ ክሪላንስ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው።
- በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀረር ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ከፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒከ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
- ሠነዳቸውን አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በአዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀረር ቅ/ፅ/ቤት ስልክ ቁጥር 0256660691/ 0913745963/0912806409
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት
