የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር 30,000 (ሰላሳ ሺ) ኩንታል የተዳመጠ ጥጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Bahir Dar Textile Share Company (የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር 30,000 (ሰላሳ ሺ) ኩንታል የተዳመጠ ጥጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ባህር ዳር ዋናው መ/ቤት ወይም አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ገዝታችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ መክፈቻው ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 (ለሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በሃያ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ዋናው መ/ቤት ግዥና አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል። በጨረታ መክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻው ዕለት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-
- ባህር ዳር:- 058 220 00 80 / 058 222 06 61
- አዲስ አበባ፡- 011 553 13 81 / 011 553 97 42 ይደውሉ
የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር
