Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
  • Address ደብረ ማርቆስ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-771-66-91
  • Websitehttp://www.dmu.edu.et/
  • Deadline15 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-16 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት አመት የተማሪዎች የምግብ ግብዓት አቅርቦት ግዥ ከዚህ በታች የተገለፁትን ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ደ/ማ/ዩ/ብግጨ/27/2017

 

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት አመት የተማሪዎች የምግብ ግብዓት አቅርቦት ግዥ ከዚህ በታች የተገለፁትን ማለትም

ሎት-1- የዳቦ ዱቄት (ለዋናው ካምፓስ)

ለት-2- የዳቦ ዱቄት (ለጤና ካምፓስ)

ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከዚህ በታች ማለትም፤

  1. በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ማለትም

ሎት-1- የዳቦ ዱቄት 100,000.00 ብር (አንድ መቶ ሺህ ብር)

ሎት-2- የዳቦ ዱቄት 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር)

  1. በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ አለበት
  2. ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  4. የጨረታውን ፋይናሽያል ዶክመንት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተከታታይ 15 ቀናት በኋላ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ይከፈታል፡፡

ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ በእለቱ ይከፈታል፡፡

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 058 771 66 91/058/178 00 37/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

 

Save Tender