አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መ/ቤት የሚገኘውን የጋራዥ ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
Agri Service Ethiopia (አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ)
የጋራዥ ቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መ/ቤት የሚገኘውን የጋራዥ ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም፣
- ድርጅቱ ለጋራዥ አገልግሎት ኪራይ የሚሆን የቦታ ስፋት 850 ካ.ሜትር ላይ 144 ካ.ሜ ሼድ የተገነባ ፤ ሁለት የመታጠቢያ ክፍሎች፣ ሶስት መጸዳጃ ቤት፣ ሁለት የመስሪያ ጉድጓድ 3ፌዝ (3 phase) የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና የተለያዩ የመስሪያ ዕቃዎች ያለው ሲሆን፣
- ተጫራቾች ዝርዝር የኪራይ ሰነድ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ከአግሪ ስርቪስ ኢትዮጵያ ሂሣብ ክፍል የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ በመውሰድ የጋራዡን ቦታ መጎብኘት ይቻላል። ስለሆነም ተጫራቾች፤
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ፣ ቲን ሰርቲፊኬት፣ ተ.ጨ.እ.ታ ምዝገባ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን ግብር አጠናቆ ለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለጨረታው ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ብር 35,000.00 /ሰላሳ አምስት ሺ ብር/ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚወዳደሩበትን የመነሻ ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ወርሃዊ የኪራይ ዋጋ በመግለጽ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎኘ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኘሮፖዛል ለየብቻ እና ሁለቱን በአንድ ፖስታ ተደርጎ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ድረስ ብቻ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ሲፒኦ ያልቀረበበት፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሌለው እና በጨረታው ሰነድ የተቀመጠውን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል።
- ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ስዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣
- ጨረታው ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት በ4፡00 ላይ በጨረታው ላይ ለመገኘት ፍላጎት ባላቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ጨረታውን ያሸነፈው አካል በ7 ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ጋር ሕጋዊ የውል ስምምነት ማድረግ ይኖርበታል።
- መድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ
የግሎባል ሆቴል በስተጀርባ አዲስ አበባ
ስልክ ቁጥር 0114-666417/0114651212
