በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ለልደታ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች እና አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በልደታ ክ/ከተማ ጤና መምሪያ የልደታ ጤና ጣቢያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የግዥው መለያ ቁጥር -004
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ---10---- አስተዳደር ለልደታ ጤና ጣቢያ የ2017 ሎቶች
- ሎት 1. የደንብ ልብስ 6211------449.29፤
- ሎት 2. የፅዳት እቃ 6218 -------2394.57፤
- ሎት 3. የደንብ ልብስ ስፌት 6211-----449.29፤
- ሎት 4. መድሀኒት 6214------2001.77፤
አሸናፊ የሚያቀርበው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ እስከ 60 ቀን ድረስ የዋጋ ለውጥ ማድረግ አይቻልም ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ። በዚህም መሰረት
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ግዥ/ አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገበ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው በካሽ ከሆነ አንቀበልም፤
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለእያንዳዳቸው ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ልደታ ጤና ጣቢያ ህንፃ 5ተኛ ላይ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ሳጥን ውስጥ ኮፒ እና ኦርጅናል ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአስረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማህተም ፤ ፊርማ ፤ ለእያንዳንዱ ሎት የተሟላ ሰነድ መኖር አለበት ፤ ዋጋው የሚሞላበት ሰነድ በመስሪያ ቤቱ በሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ መሆን አለበት እና እያንዳንዱ ተጫራች ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በገዛው ሎት ልክ ነው ማለትም አንድ ከገዛ አንድ እንጂ በአንድ ሎት 2-3 መወዳደር አይቻልም።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ
በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የልደታ ጤና ጣቢያ ከልደታ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ምርታማነት ማሻሻያ ጸበሉ ጎን
የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር --- 011 5-58-20-61 ወይም 011 5-58-49-66
በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የልደታ ጤና ጣቢያ
