የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ ለገሐር አካባቢ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሕንፃ ምድር ወለል ላይ የሚገኘውን እና በደቡብ ዲስትሪክት (መስቀል አደባባይ ላይ የሚገኘው ልዩ ስሙ በአንበሳ ሕንፃ) ስድስተኛ ፎቅ ላይ ያሉ ባዶ ክፍሎች ለንግድ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢአጽ/
ግንአዳ/016/2017
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ ለገሐር አካባቢ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሕንፃ ምድር ወለል ላይ የሚገኘውን እና በደቡብ ዲስትሪክት (መስቀል አደባባይ ላይ የሚገኘው ልዩ ስሙ በአንበሳ ሕንፃ) ስድስተኛ ፎቅ ላይ ያሉ ባዶ ክፍሎች ለንግድ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
- ድርጅታችን ለኪራይ ያቀረባቸውን ክፍሎች በጨረታ መወዳደር/ መሳተፍ የሚፈልግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 9:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ክፍል በኢትዮጵያ መድን ድርጅት (Ethiopian Insurance Corporation) ስም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ወይም ለዘጠና ቀናት በሚቆይ ቅድመ ሁኔታን ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሽገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሰኔ 04 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ሰኔ 04 ቀን 2017 ዓ.ም. በድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር፡-011-5512400 የውስጥ መስመር 237/262
ወይም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኢትዮጵያ መድን ድርጅት
