በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችን ፣ የፅዳት ዕቃዎችንና የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ ጤና ጣቢያ
3ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችን ፣ የፅዳት ዕቃዎችንና የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት የሚያገለግል ብር 3000.00 (ሶስት ሺ ብር) በድርጅቱ ስም ሲፒኦ (CPO) በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻችው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈራረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በየካ ጤና ጣቢያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ ቡድን በመገኘት ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ስርዙ ጎን ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት በ7 የስራ ቀናት ውስጥ የመደበኛ ውል ሰነድ መፈራረም ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ የሚያጋጥመው ከሆነ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
የካ ጤና ጣቢያ ሾላ ገበያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
ስልክ:- 011 893 29 82/011 667 42 37
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ ጤና ጣቢያ
