Tender Detail

Tender Details

  • Company የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የወሊሶ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ወሊሶ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 341 0905
  • Website
  • Deadline07 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-07 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የወሊሶ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የወሊሶ ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የወሊሶ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት፡-

  1. ቤቱ ሙሉ ግቢ ወይም ህንፃ ሆኖ አጠቃላይ ስፋት ከ250ካሬ ያላነሰ እና ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት አመቺ የሆነና ለዋናው መንገድ ቅርብ የሆነ::
  2. የጽ/ቤቱን ሠራተኞች እና ተገልጋዮች ከሚያውኩ የድምጽ ብክለት የራቀ እንዲሁም አጎራባች ቤቶች እና ህንፃ ውስጥ የቢሮ አገልግሎት ከሚያውኩ ሁኔታዎች የሌለው።
  3. የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ያለው::
  4. ዓመታዊ ግብር የተከፈለ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ::
  5. የራሱ የሆነ መፀዳጃ ቤትና የጥበቃ ቤት ያለው::
  6. የራሱ የሆነ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ, የውሃ እና የስልክ መስመር ያለው::
  7. የሚያከራየውን ቤት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር ዋጋ ማቅረብ የሚችል እና ለ3 ዓመት ውል ለመግባት ፈቃደኛ የሆነ
  8. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ከአስተዳደሩ ወሊሶ ቅ/ጽ/ቤት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ወሊሶ ቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን መመለስ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመሠረዝ ይችላል። ተጫራቾች ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ ክፍሎችን ብዛት እና ስፋት በግልጽ በካሬ ሜትር በማስፈር የአንድ ካሬ ሜትር ኪራይ ዋጋ ከተ.ዕ.ታ ጋር በማስላት አጠቃላይ ዋጋውን በካሬ በማብዛት በተዘጋጀው ሰንጠረዥ ውስጥ መገለጽ አለበት።

ለበለጠ መረጃ 011 341 0905 እና 011 366 4271

 

የመግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የወሊሶ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender