Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ አካባቢ በሚገኛው አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ህንፃ 15ኛ ፎቅ የሰፕላይ ቼይን እና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-38-98
  • Websitehttp://www.ethiopianelectricutility.gov.et/
  • Deadline12 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-12 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያየ መጠን ያላቸው ባንዲራዎች እና ተያያዥ ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፍፋግ/ግጨ-020/2017

 

ተቋማችን የተለያየ መጠን ያላቸው ባንዲራዎች እና ተያያዥ ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

የተለያየ መጠን ያላቸው ባንዲራዎች እና ተያያዥ ህትመቶች

200,000.00

ሰኔ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ሰኔ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. ተቋማችን ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ስለጀመረ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች በመያዝ ወደ ተቋማችን ቢሮ ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በአካል በመቅረብ መለያ ስም እና የሚስጥር ቁጥር ለመውሰድ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚስጥር ቁጥራቸውን ከወሰዱ በኋላ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ባንክ የከፈሉበትን የክፍያ ሰነዱን ስካን በማድረግ misrakfan@ gmail.com ወይም getu3010@gmail.com በሚል ኢሜይል አድራሻ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. በመቀጠል በተቋሙ የዌብሳይት አድራሻ https://eeusrmvendorportal ethiopianelectricutility et/irj/portal ላይ በተሰጣቸው መለያ ስም እና የሚስጥር ቁጥር በመግባት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ ያገኘ ተጫራች የኤሌክትሮኒክስ ዘዴን በመጠቀም ምላሽ ለመስጠት ተቋማችን በሚያመቻቸው የስልጠና /training orientation/ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ስልጠናውን በመውሰድ መሆን ይኖርበታል፡፡
  6. አድራሻ:- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር 011-126-66-05/011-156-01-48::
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና "ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY" በሚል መሆን ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የኤሌክትሮኒክስ ግገዢ የምላሽ አሰጣጥ ስርአትን በመከተል ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት መሆን ይኖርባቸዋል፤
  9. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ የኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርአትን በመከተል በኦንላይን ስለሚሆን በተራ ቁጥር 4 በተገለጸው መሰረት በኦን ላይን ይሆናል፡፡
  10. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

 

Save Tender