Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ
  • Address ልደታ ክ/ከተማ አብነት ጤና ጣቢያ ከአብነት አደባባይ ፊት ለፊት ግቤ ህንፃ ጎን 100 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-273-43-49
  • Website
  • Deadline05 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-06-05 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለፁት መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ፡- ሎት 01 የደንብ ልብስ /የዶክተር ጫማ/ ግዥ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 06/2017

 

በልደታ /ከተማ ጤና /ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ 2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለፁት መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ፡- ሎት 01 የደንብ ልብስ /የዶክተር ጫማ/ ግዥ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት //አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢያዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን /TIN/ እና የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ መወዳደር የሚችሉት ባመረቱት ምርት ብቻ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ካደራጃቸው ተቋም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000 (ሶስት ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. አሸናፊ ተጫራቾች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው
  5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል በአብነት ጤና ጣቢያ 1 ፎቅ የግዥ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአብነት ጤና ጣቢያ 1 ፎቅ የግዥ ፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 230 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 300 ሰዓት በአብነት ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ዉጭና ከቫት ጋር እና ጠቅላላ ዋጋ ከቫት ጋር ያለውን ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸዉ ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. /ቤቱ ለጨረታ ካቀረባቸው እቃዎች ውስጥ እስከ 20% ድረስ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ጥያቄ በስልክ ቁጥር፡- 011-273-43-49/39/59 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡- ልደታ /ከተማ አብነት ጤና ጣቢያ ከአብነት አደባባይ ፊት ለፊት ግቤ ህንፃ ጎን 100 ሜትር ገባ ብሎ

 

በልደታ /ከተማ ጤና /ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ

 

Save Tender

በኮ/ቀ//ከ/ወ/6/ሚ/ጣቢያ በጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎችን፣ የጥገና ስራዎች...

READ MORE
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለ2019 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡-

READ MORE