የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEP/TSO/NCB/09/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፣ ሰው ሀብትና ፋይናንስ አስተዳደር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ገንዘብ ያዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ግዥ ቢሮ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TSO/NCB/09/2017 የሚል ምልከት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በሰንጠረዡ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም የተዘጋጀ በማቅረብ አቅርቦት ግዥ መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
Tyer 8.25 R 20 ግዥ |
ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) |
ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 58 19 16/011-5 58 17 25 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
