Tender Detail

Tender Details


የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ሽሮ ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ያለውን የገበያ ማዕከል ለተለያዩ ንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በግልጽ ጨረታ የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡


 

የንግድ ቤቶች ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- ግጨ 001/2017

 

የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ሽሮ ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ያለውን የገበያ ማዕከል ለተለያዩ ንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በግልጽ ጨረታ የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ተጫራቾች:-

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚያስፈልግ ሲሆን በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይቻልም፡፡
  2. ከ12 ወር ለበለጠ ጊዜ ቅድሚያ ለሚከፍል ተከራይ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
  3. ተከራይና አከራይ በህጉ መሠረት ውል ይዋዋላሉ፡፡
  4. በጨረታ ያሸነፉበትን ቦታ /ቤት/ ለሌላ ማከራየት አይቻልም፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በሽሮ ሜዳ እና በድርጅቱ ዋናው መስሪያ ቤት ሽያጭ መደብሮች ሰነድ በመግዛት ተጫራቾች በአካል በሽሮ ሜዳ በአሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት ተገኝቶ ቦታውን ህንጻውን መመልከት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማሸግ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 67 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ከዋናው መግቢያ በር ጀምሮ ማዕከሉ ለ3 ብሎኮች የተከፈለ እና ሶስት ዓይነት አገልግሎት እንዲሰጡ የተወሰነ ሲሆን

እነሱም፡-

    1. ብሎክ 1 ለባንኮች እና መሰል አገልግሎቶች፣
    2. ብሎክ 2 ለባልትና፣ ለሱፐር ማርኬት፣ ለጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሸቀጣ ሸቀጥ እና መሰል፣
    3. ብሎክ 3 ለሀገር ባህል ልብሶችና አልባሳት መሸጫ አገልግሎት የሚውል መሆኑን በመረዳት ከባንክ እና መሰል ድርጅቶች ውጭ ስታንዳርዱ 4×4 ካሬ ሜትር ሆኖ ዝቅተኛው መወዳደር የሚቻለው መጠን 2×4 ካሬ ሜትር ለአንድ ዓይነት ንግድ ሥራ ታሳቢ በማድረግ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  1. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ :- 0911-99-98-51/0911-04-32-12

አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር ገባ ብሎ ወይም /FOA/ አጠገብ አና ሽሮ ሜዳ አሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ሽያጭ መደብር፣

 

የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት

 

Save Tender