ድርጅታችን ለከተማው መጠጥ ውሃ አገልግሎት ሠራተኞች የሚውሉ የደንብ ልብሶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የባቱ አዳሚ ቱሉ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 2/2017
ድርጅታችን ለከተማው መጠጥ ውሃ አገልግሎት ሠራተኞች የሚውሉ
1ኛ. የደንብ ልብሶችን
በመሆኑም ከታች የተጠቀሱት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፋ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት የባቱ አዳሚ ቱሉ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አስር ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋና ጠቅላለውን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻና የጨረታውን ዓይነት በመጥቀስ የባቱ አዳሚ ቱሉ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በዕለቱ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቢሮ ውስጥ ይሆናል፡፡
- አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ድርጅቱ ድረስ በማቅረብ ዕቃው ትክክለኛነቱ በባለሙያ ሲረጋገጥ ክፍያ የሚከፈለው መሆኑን የሚስማማ መሆን አለበት፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ፣ በስልክ ቁጥር 0464412497/0461411253 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የባቱ አዳሚ ቱሉ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
