Tender Detail

Tender Details

  • Company የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይን ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት
  • Address ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አደባባይ ፊት ለፊት የአስተዳደሩ ህንጻ በሚገኝበት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118-83-80-20
  • Website
  • Deadline24 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-26 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት በስፖርት ጽ/ቤት ለሚተዳደሩ የስፖርት ሜዳ ዙርያ ሱቅ ኪራይ አገ/ት ግዥ ለመፈጸም በድጋሚ የወጣ ጨረታ ሲሆን ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይን ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት


 

በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር 002/2017

 

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት በስፖርት ጽ/ቤት ለሚተዳደሩ የስፖርት ሜዳ ዙርያ ሱቅ ኪራይ አገ/ት ግዥ ለመፈጸም በድጋሚ የወጣ ጨረታ ሲሆን ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ሲሆኑ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያውን ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

 

ተ.ቁ

የሎት አይነት

መግለጫ

የሲ.ፒ.ኦ መጠን በብር

1

ሎት -1

የስፖርት ሜዳ ዙርያ ሱቅ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

50,000.00

 

  1. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር ዐ2 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጂናልና ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማደራጀት ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ህንጻ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን በሚገኝበት 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛው ቀን 11፡00 ሰአት ድረስ አየር ላይ ውሎ በማግስቱ በ11ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ይከፈታል ።
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የአገልግሎት ግዥዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  5. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ

አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አደባባይ ፊት ለፊት የአስተዳደሩ ህንጻ በሚገኝበት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን

ስልክ ቁጥር ፡- 0118-83-80-20

 

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች

 

Save Tender