የአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 11 - የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ እና ሎት 12፡- የላፕቶፕ ኮምፒዩተር ግዥ ጨረታ ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: ACBO/NCB/G/04/2017
የአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 11 - የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ እና ሎት 12፡- የላፕቶፕ ኮምፒዩተር ግዥ ጨረታ ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ማንኛውም ተጫራች
- በዘርፉ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት እና ታክስ ክሊራንስ (የታደሰ) እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት-11 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) እና ለሎት-12 ብር 6,000.00 (ስድስት ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እውቅና ከተሰጣቸው ባንኮች የተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ የኢትዮጵያ ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህንጻ ቁጥር 2 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ክፍል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህንጻ ቁጥር 2 ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን በበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በጨረታ መክፈቻው ዕለት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ሂደቱን እያስተጓጉልም፡፡
አሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህንጻ ቁጥር 2
የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ሥራ ክፍል
ለበለጠ መረጃ 057-448-3074/057-448-3144
አሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
