መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር ባሠራው መርካቶ መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ የገበያ ማዕከል ውስጥ 5ኛ ፎቅ ላይ ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል /ለሱቅ ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት/ የሚውል ቦታን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር
ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል የሕንፃ ቦታ ኪራይ
የጨረታ ማስታወቂያ
መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር ባሠራው መርካቶ መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ የገበያ ማዕከል ውስጥ 5ኛ ፎቅ ላይ ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል /ለሱቅ ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት/ የሚውል ቦታን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10 ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት የማኅበሩ ሕንፃ በሚገኝበት 4ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር M433 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0112-313147/0112-313237/0118-722926 ወይም በአካል ሲዳሞ ተራ መተሳሰብ ለዕድገት የገበያ ማዕከል መጠየቅ ይቻላል፡፡
መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር
