በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ያገለገሉ የተለያዩ የስፌት ማሽኖች፣ ኮምፕሬሰሮች እና የተለያዩ ጨርቃ ጨርቆችና አልባሳቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ያገለገሉ የተለያዩ የስፌት ማሽኖች ፣ ኮምፕሬሰሮች እና የተለያዩ ጨርቃ ጨርቆችና አልባሳቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የተገበረበት ንግድ ፈቃድ ፤ ቫት ተመዝጋቢ ታክስ ፤ ከፋይ የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታው መወዳደሪያ ዋጋ ጋር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ሰነዶች ህጋዊ ንግድ ፈቃዶች እና ታክስ ከፋይ ሰነዶችን ይጨምራል እና ፋይናንሻል መግለጫ በፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዶቹ የድርጅታቸው ማህተምና የኃላፊው ፊርማ ያለበት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በኮሚቴው ሰብሳቢ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ዝርዝርሩን ከጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 20 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ21ኛው ቀን በ7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ8፡30 ሰዓት በኢንዱስትሪያችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን 21ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጁትን በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ /አዳማ/ በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ።
- ኢንዱስትሪው የተሻሉ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከወንጂ ማዞሪያ ወደ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ 5 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ
በስልክ ቁጥር፡- 09-10-73-78-72/ 09-18-32-49-47
አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
